A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ እንደ ንብ ቀስሞ እንደ ወጥ ቀምሞ እንደ ንጉሱ አጎንብሱ እንደ ወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅሎ እንደ ወንድማማች ተበዳደሩ እንደ ባእዶች ተቆጣጠሩ እንደ ወይን መልምዬ እንደ እንጨት ተክዬ እንደ ውሀ ይፈስ እንደ ጋዝ ይነፍስ እንደ ውሌ ደጃዝማች ባሌ እንደ ዝንጀሮ በአፋፍ አንደ ጦጣ በዛፍ አንደ ዳኛ በውል አንደ ምሰሶ በመሃል እንደ ገና ይመታል በገና እንደ የቤቱ ብዙ ነው ብልሀቱ እንደ ጸሀይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ አንደ አበባ ያሸበረቀ አንደ ጴጥሮስ ብጽላሎተ ርአስ አንደ ጳውሎስ በዘፈረ ልብስ እንደ ፈረስ ጆሮ እንደ ሰላጢን ጉሮሮ እንደ ፈታሂነቱ ሁላችን እንኮነናለን እንደ መሃሪነቱ ሁላችን እንማራለን እንዲህ ሊታረፈን ለሚስቴ ነፈግኋት እንዲህ ልጠግብ በሬዬን አረድኩት እንዲህ ነድጄ ልሙት የፊቱን በኋላ አድርጎት እንዲያውም በመላ ፈስ ዳለቻ ነው እንዲያው ብትመለሺ የገንፎ እንጨት ላሺ Previous1234567891011121314151617181920212223242526272829303132333435363738394041424344454647484950515253545556575859606162636465666768697071727374Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra