A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ጸሀይ ሳለ ሩጥ አባት ሳለ አጊጥ ጸሀይ ብልጭ ወፍ ጭጭ ሲል ጸሀይ ካልወጣ ከሰፈረበት አይነሳ አንበጣ ሴት ምክንያት አታጣ ጸሀይ የጠዋት አዱኛ የሽበት ጸሀይ ያየውን ሰው ሳያየው አይቀርም ጸሀይና ንጉስ ሳለ ሁሉም አለ ጸሎት በጽሞና ነገር በደመና ጸሎት በፍቅር ሀይማኖት በምግባር ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከምግባር ይበጃል ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከግብር ጸሎት ያለፍቅር ሀይማኖት ያለግብር ኣይረባም ጸጸት እያደር ይመሰረት ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ ሀጥኣን ግን በተቃጠሩበት ይተጣጣሉ ጽዋ በተርታ ስጋ በገበታ ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ ጽድቁ ቀርቶብኝ በውሉ በኮነነኝ ጽድቅ ለመንኳሽ ቀኝ ለከሳሽ ጽድቅ አንደ ላሊበላ እድሜ አንደ ማቱሳላ ይስጥህ ጽህፈት በብራና ዘፈን በበገና 12 Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra