A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ በሃምሌ ጎመንና አሞሌ በሀምሌ ጤፍ ይዘሩ ቤት ይሰሩ በለፈለፉ በአፍ ይጠፋ በልቶ የማይበርደው የሰው ነገር የማይከብደው ሁለቱ አንድ ነው በልጁ ቆዳ ተጠቅልሎ የተቀበረ የለም በመስከረም ሊያብድ ያለ ክረምቱ ላይ ጨርቁን ይጥላል በሙቅ ውሀ የታጠበ በሰው ገንዘብ የቸረ በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ በሞኝ ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ይለኩበታል በራቸውን ክፍት ትተው ሰውን ሌባ ነው ብለው ያማሉ በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሞኙ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ እልም ካለው ገደል ወደቅክብን ወይ በሬ ቅባቱን በቅልጥሙ ይዞ ይኖራል ለምንህ ቢሉት ኋላ ለገዛ ቁርበቴ ማልፊያ ይሆነኛል አለ በሬ ካራጁ ቢላ ተዋሰ በሬ ካራጁ ይውላል በርበሬን ከላመ ከሞተ አግኝተሽው ዋጥ ስልቅጥ አድርገሽ ከምኔው ጨረሽው በሰው ምድር ልጇን ትድር በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም በሴትና በውሀ የማይርስ የለም 1234567Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra