A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ኣባቱን ሳይመስል የተወለደ ልጅ ከጎረቤት ያሳማል አባቱን አያቅ አያቱን ናፈቀ አባቱን የጠላ የሰው አባት ይሰድባል አባቱን ያላወቀ አያቱን ናፈቀ አባቱ ያልበላውን ኑግ ልጁ አማረው ቅባ ኑግ አባት ሳለ አጊጥ ጀምበር ሳለ ሩጥ ኣባቱን የጠላ የስው አባት ይስድባል አባቱ ያልበላውን ኑግ ልጁ አማረው አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው አባቱን ረስቶ ላማቱ ይነጭ አማቱን ገድሎ እናቱን ያስፈጭ ኣባቱን ረስቶ ላማቱ ይነጭ አማቱን ጋርዶ እናቱን ያስፈጭ አባቱን ገድሎ ላማቱ ይነጭ አማቱን ገድሎ እናቱን ያስፈጭ አባቱን ገድሎ ላማቱ ይነጭ አማቱን ጋርዶ እናቱን ያስፈጭ ኣባቴ ሲሞት እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው አባቴ ትንሽ ነው ብልቴ ትልቅ ነው የሚል የለም ኣባት ሲታማ ልጅ አይስማ አባት አይከሰስ ሰማይ አይታረስ ውሀ አይጠበስ አባት በነውሩ ይከሰሳል ሰማይ በመብረቅ ይታረሳል ውሀ በምንቸት ይጠበሳል አባት ካነሰው ምግባር ያነሰው አባት የሌለው ልጅ መዝጊያ የሌለው ደጅ Previous1234567891011121314151617181920212223242526272829303132333435363738394041424344454647484950515253545556575859606162636465666768697071727374Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra