A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ወጪ ያዘዘባት ጥቁር ሴት አንገቷን ትነቀሳለች ወጭትና ሴት ሲከናነቡ ይሻላል ወፍ እንዳገርዋ ትጮሀለች ወፍጮና ሴት መቼም አይሞላለት ዋቢ ያለው ያመልጣል ዋቢ የሌለው ይሰምጣል ውሀ ለሚወስደው ሰው በትርህን እንጂ አጅህን አትስጠው ውሀ ለቀደመ ግዳይ ለፈለመ ውሀ ለወሰደው ካሳ አይከፍልም ውሀ ለወሰደው ፍለጋ የለውም ውሀ ሊያንስ ሲል ይገማል ሰው ሊያንስ ሲል ይኮራል ውሀ ላነቀው ባለቤቱ ላላወቀው መድሀኒት የለውም ውሀ ልትቀዳ ሄዳ አንስራዋን ረስታ መጣች ውሀ መልሶ ውሀ ቀልሶ ውሀ መመለስ ወደ ሌላ ማፍሰስ ውሀ ምን ያስጮኸዋል ድንጋይ ውሀ ምን ያገሳ ድሀ ምን ያወሳ ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው ውሀ ሲደርቅ ይሸታል ሰው ሲከዳ ይወሽክታል ውሀ ሲጎድል ተሻገር ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ በለዘብታ ድንጋይ ይፈነቅላል Previous12345Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra