A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ወንድ ከዋለበት ከብት ከተስማራበት ወዛም ገማ ቢለው የነጭ ወሬ ነው አለው ወይ አበዳሪ ወይ ተበዳሪ ይሞታል ወይ አታምር ወይ አታፍር ወይዘሪትነት ያንድ ቀን ርቀት ወይ ዘንድሮ !አለች ቀበሮ ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ወደሽ ነው ቆማጢት ንጉስ ትመርቂ ወደቀ ሲሉ ተሰበረ ነው ወደው የዋጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም ወዳጅ ይመጣል ከራያ ጠላት ይወጣል ከጉያ ወገኛ ቀበሌ ወረዳ (ከፍተኛ ) መሆን ያምራታል ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ወጠጤ ለወጠጤ ቢማከሩ አንዳይታረዱ ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥ ወጣ ወጣና እንደ ሽንበቆ ተገነደሰ እንደ ሙቀጫ ወጥን ማን ያውቃል ቢሉ ቀላዋጭ ወጥን የሚጨርስ መጎራረስ ሴትን የሚያስመታት መመላለስ ወጪ ያዘዘባት ጥቁር ሴት አንገቷን ትነቀሳለች Previous12345Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra