A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ሽማ ለብሶ ስልቻ በቅሎ ጭኖ ለብቻ ሽማ ማዋስ ለባላገር በቅሎ ማዋስ ለወታደር ሽማ በውሀ ሰው በንስሀ ሽማን በውሀ ሰውነትን በንስሀ ሽማ በየፈርጁ ይለበሳል ሽማና ምስጥ ወደ ውስጥ ሽማኔ በመኑ ጠይብ በከሰሉ ሽማኔ በድሩ ጠይብ በመንደሩ ሽማኔ ድውሩን ባለስልጣን ክብሩን ሽማን ጠምዞ ያሰጧል አህልን አላምጦ ይበሏል ሽምበቆ በመርዘሙ አይሆንም ምሰሶ ሽምበቆ በመርዘሙ ምሰሶ አይሆንም ሽርሙጣ ስታረጅ አቃጣሪ ትሆናለች ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ አበደ ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ ያበደ ሽኚና ጥላ ቤት ኣይገባም ሽኚ ቤት አያደርስም ሽኝ ቤት አይገባም ሽክላ ቢጥሉት ገለባ ሹመት ላወቀው ይከብደዋል ላላወቀው ያሳብደዋል 12345Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra