A collection of common Amharic Proverbs. የአማረኛ ተረትና ምሳሌዎች። Browse Amharic proverbs alphabetically or search using your own keywords. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ለቅዘን እግር አንስተውለት ለውሻ ሮጠውለት ለቆመ ሰማይ ቅርቡ ነው ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት ለበራ ወለባ ለውሻ ገለባ ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ ለበግ ደጋ ለምቾት አልጋ ለቡናሽ ቁርስ የለሽ ለነገርሽ ለዛ የለሽ ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ ለቤት ሳንቃ ለሰው አለቃ ለቤት ሳንቃ ለነገር ጠበቃ ለቤት ባላ ለችግር ነጠላ ለብልህ ንገረው ምን ይስተው ብዬ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ ለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ ለብልህ አይነግሩ ላንበሳ አይመትሩ ለብልህ አይነግሩ ለንጉስ አይመክሩ ለብልህ አይነግሩም ለንጉስ አይመክሩም ለብልህ አይነግሩ ካልጠየቀ በስተቀር ለተማሪ ቆሎ ለወታደር በቅሎ ለተሟጋች መዘዘኛ የዳኛ ትእግስተኛ Previous12345678910111213141516171819202122Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra